ስለ አባልነት

አንቀጽ 26: የማህበሩ አባል ስለመሆን

  1. እደሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፤ በህግ መብቱ ያልተገፈፈ የማህበሩን ዓላማ የሚደግፍና በሕግና በዚህ ደንብ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ የማህበሩ አባል መሆን ይችላል፡፡
  2. የማህበሩ አባል ለመሆን የጽሑፍ ማመልከቻ ማሰገባት ማህበሩ የሚያዘጋጀውን የአባልነት ማመልከቻ ቅፅ መሙላት ያስፈልጋል፡፡
  3. በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰኑ የአባልነት በየጊዜው ስምምነት የሚያደርጋቸውን ክፍያዎችና መዋጮዎች መክፍል የሚችል፡
  4. ማህበሩ 5 ዓይነት አባላት ይኖሩታል፤እነርሱም ሙሉ አባል፤ተባባሪ አባል፤ተቋማዊ አባል፤የክብር አባልና የተማሪ አባል ናቸው፡፡

አንቀጽ 27 : የአባልነት መስፈርቶች                                        

  1. በመሬት አስተዳደርና ቅየሣ፤መሬት እቅድና አጠቃቀም፤የመሬት ሃብት ግመታ በማይንቀሳቀስ ንብረት ሕግ ወይም ሌሎች ከመሬት አስተዳደር ጋር ግንኙነት ባላቸው ሞያዎች የመጀመሪያ ድግሪና በላይ ያለው፤ወይም
  2. ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ዲፕሎማ ወይም ተመጣጣኝ የት/ት ደረጃ ያለው ሆኖ የ2 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው ወይም የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ባይኖረውም በመሬት ጉዳይ ላይ ተገቢውን ምርምር ያደረገ ከሆነ ፤ እና
  3. ማህበሩ የሚያስቀምጠው ተጨማሪ  መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የማህበሩ አባል መሆን ይችላል፡፡
  4. ሆኖም የማህበሩ ምስረታ በዓል ቀናት የተሳተፈ ማንኛውም ግለሰብ በመሬት አስተዳደር ስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሰፊ ልምድ ያለውና ማህበሩን ለመደገፍ ቁርጠኛ የሆነ ሰው የአባልነት ጥያቄ ሲያቀርብ መስራችና ሙሉ አባል ይሆናል፡፡

አንቀጽ 28: የአባላት መብት

  1. ሁሉም ሙሉ አባላት ማህበሩን በተመለከቱ ጉዳዩች ላይ እኩል መብት አላቸው፡፡
  2. የማህበር አባልነት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው፡፡
  3. ማንኛውም የማህበሩ ሙሉ አባል፡-

ሀ/ ለማህበሩ ዓላማና ተልእኮዎች መሳካት የሚጠቅሙ ማናቸውም አይነት ስራዎች የመስራት፤

ለ/ የመምረጥ፤የመመረጥና ስለማህበሩ እንቅስቃሴ ማንኛውንም መረጃ ጠይቆ የማግኘት፤

ሐ/ በጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ የማገኘት፤ስለማህበሩ እንቅስቃሴ አስተያየትና ድምጽ የመስጠት፤እና

መ/ “አባልነቱ እንዲቋረጥ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በጠቅላላ ጉባኤው የመሰማት መብት አለው

አንቀጽ 33: የአባልነት ግዴታ

ከክብር አባላት ወጪ ያሉ ሁሉም የማህበሩ አባላት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሯቸዋል፡-

  1. የማህበሩን የመተዳደሪያ ደንብ የማክበር
  2. ማህበሩን ለማሻሻል ለሚደረገው ጥረት በምርምር ሆነ በሌላ መንገድ ሁሉ የመሣተፍ፤እንዲሁም ከፍተኛውን የሙያ ሥነ-ምግባር በመከተል የማህበሩን ዝናና መልካም ስም የመጠበቅ፤
  3. ማህበሩ በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ የመሳተፍ፤
  4. በማህበሩና በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውሳኔዎች የመገዛት፤እና
  5. የማህበሩን የመመዝገቢያ ክፍያና የአባልነት መዋጮ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ጉባኤው የሚወስናቸውን ሌሎች ክፍያዎች በወቅቱ የመክፍል ግዴታዎች ናቸው፡፡