የኢትዮጵያ መሬት አስተዳደር ባለሞያዎች ማህበር ከተቋቋመበት ዓላማዎች አንዱ በመሬት ዘርፍ ላይ የሚሰሩን ባለሙያዎች አቅም መገንባት ነው።Read More
ስለሆነም በሐገራችን ወጥ የሆነ የመሬት ፖሊሲ አቀራረጽ ስርዓትን ለማገዝ ለሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን አቅም ግንባታ መስጠት አስፈላኢ ሁኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የኢትዮጵያ መሬት አስተዳደር ባለሞያዎች ማህበር ከ USAID – LGA (Land Governance Activity) ጋር በመተባበር በመሬት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ደብረዳሞ ሆቴል ለተከታታይ አምስት ቀናት (ከ01 – 05/2016 ዓም) ለመስጠት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። የስልጠናዉም ተሳታፊዎች ከሁሉም የሃገራችን ክፍሎች የመጡ ሲሆን በሁሉም የመሬት ነክ ዘርፎች ላይ እየሰሩ ያሉ ባለሙያዎች ናቸው።
ስልጠናዉን ለማስጀመር የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አቻምየለህ ጋሹ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ መሬት አስተዳደር ባለሞያዎች ማህበር አመሰራረትና አሁን ያለበትን ደረጃ ለተሳታፊዎች አስረድተዋል። ቀጥለዉም ይህ ስልጠና ፈርጀ ብዙ የሆኑ ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ችግሮች መፍታት እንደሚያስችልም ተናግረዋል። በመጨረሻም አሰልጣኞቹ በመሬት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አቅምና ልምድ ያላቸው መሆኑን ገልጸው ስልጠናዉን በይፋ ከፍተዋል።