ስለ አባልነት
አንቀጽ 26: የማህበሩ አባል ስለመሆን
- እደሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፤ በህግ መብቱ ያልተገፈፈ የማህበሩን ዓላማ የሚደግፍና በሕግና በዚህ ደንብ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ የማህበሩ አባል መሆን ይችላል፡፡
- የማህበሩ አባል ለመሆን የጽሑፍ ማመልከቻ ማሰገባት ማህበሩ የሚያዘጋጀውን የአባልነት ማመልከቻ ቅፅ መሙላት ያስፈልጋል፡፡
- በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰኑ የአባልነት በየጊዜው ስምምነት የሚያደርጋቸውን ክፍያዎችና መዋጮዎች መክፍል የሚችል፡
- ማህበሩ 5 ዓይነት አባላት ይኖሩታል፤እነርሱም ሙሉ አባል፤ተባባሪ አባል፤ተቋማዊ አባል፤የክብር አባልና የተማሪ አባል ናቸው፡፡
አንቀጽ 27 : የአባልነት መስፈርቶች
- በመሬት አስተዳደርና ቅየሣ፤መሬት እቅድና አጠቃቀም፤የመሬት ሃብት ግመታ በማይንቀሳቀስ ንብረት ሕግ ወይም ሌሎች ከመሬት አስተዳደር ጋር ግንኙነት ባላቸው ሞያዎች የመጀመሪያ ድግሪና በላይ ያለው፤ወይም
- ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ዲፕሎማ ወይም ተመጣጣኝ የት/ት ደረጃ ያለው ሆኖ የ2 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው ወይም የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ባይኖረውም በመሬት ጉዳይ ላይ ተገቢውን ምርምር ያደረገ ከሆነ ፤ እና
- ማህበሩ የሚያስቀምጠው ተጨማሪ መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የማህበሩ አባል መሆን ይችላል፡፡
- ሆኖም የማህበሩ ምስረታ በዓል ቀናት የተሳተፈ ማንኛውም ግለሰብ በመሬት አስተዳደር ስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሰፊ ልምድ ያለውና ማህበሩን ለመደገፍ ቁርጠኛ የሆነ ሰው የአባልነት ጥያቄ ሲያቀርብ መስራችና ሙሉ አባል ይሆናል፡፡
አንቀጽ 28: የአባላት መብት
- ሁሉም ሙሉ አባላት ማህበሩን በተመለከቱ ጉዳዩች ላይ እኩል መብት አላቸው፡፡
- የማህበር አባልነት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው፡፡
- ማንኛውም የማህበሩ ሙሉ አባል፡-
ሀ/ ለማህበሩ ዓላማና ተልእኮዎች መሳካት የሚጠቅሙ ማናቸውም አይነት ስራዎች የመስራት፤
ለ/ የመምረጥ፤የመመረጥና ስለማህበሩ እንቅስቃሴ ማንኛውንም መረጃ ጠይቆ የማግኘት፤
ሐ/ በጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ የማገኘት፤ስለማህበሩ እንቅስቃሴ አስተያየትና ድምጽ የመስጠት፤እና
መ/ “አባልነቱ እንዲቋረጥ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በጠቅላላ ጉባኤው የመሰማት መብት አለው
አንቀጽ 33: የአባልነት ግዴታ
ከክብር አባላት ወጪ ያሉ ሁሉም የማህበሩ አባላት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሯቸዋል፡-
- የማህበሩን የመተዳደሪያ ደንብ የማክበር
- ማህበሩን ለማሻሻል ለሚደረገው ጥረት በምርምር ሆነ በሌላ መንገድ ሁሉ የመሣተፍ፤እንዲሁም ከፍተኛውን የሙያ ሥነ-ምግባር በመከተል የማህበሩን ዝናና መልካም ስም የመጠበቅ፤
- ማህበሩ በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ የመሳተፍ፤
- በማህበሩና በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውሳኔዎች የመገዛት፤እና
- የማህበሩን የመመዝገቢያ ክፍያና የአባልነት መዋጮ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ጉባኤው የሚወስናቸውን ሌሎች ክፍያዎች በወቅቱ የመክፍል ግዴታዎች ናቸው፡፡