የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት ቢሮ ከኢትዮጵያ የመሬት አስዳደር ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር ከ USAID Land Governance Activity በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ንብረት በሚለቀቅበትና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቁሙበትን ሁኔታ ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁ.1161/2011፤ደንብ ቁ.472/2012 እንዲሁም በክልሉ የካሳ አከፋፈል መመሪያ ቁ.44/2013 ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና በደብረ ታቦር ከተማ እየተሰጠ ሲሆን ከስልጠናውም በኋላ ሰልጣኞቹ የተሻለ ግንዛቤ በማግኘት በተግባር የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚችሉና ሌሎች የካሳ ትመና ስራ የሚሰሩ ባለሙዎችን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እንደሚሰሩ ይጠበቃል፡፡ በስልጠናው መክፈቻ ላይም የአብክመ መሬት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በካሳ ትመና ላይ የተለያዩ ክፍተቶች መኖራቸውን አብራርተው ይህም ስልጠና እነዚህ ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚያስችል አመላክተዋል፡፡

በመቀጠልም ዶ/ር አቻምየለህ ጋሹ ፤ የኢትዮጵያ መሬት አስተዳዳር ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት በስልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት ስለ ማህበራችን አጭር ገለጻ ካደረጉ በኋላ የስልጠናውን አስፈላጊነት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም USAID Land Governance Activity በመወከል የተገኙት አቶ አበበ ሙላቱ በስልጠናው መከፈቻ ላይ በመገኘት ስልጠናውን ለመስጠት የነበረውን ሂደት እና ስለ ስልጠናው ወቅታዊነት አስረድተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *